Podchaser Logo
Home
የመንታ እናት ፖለቲካ !

የመንታ እናት ፖለቲካ !

BonusReleased Friday, 5th May 2023
Good episode? Give it some love!
የመንታ እናት ፖለቲካ !

የመንታ እናት ፖለቲካ !

የመንታ እናት ፖለቲካ !

የመንታ እናት ፖለቲካ !

BonusFriday, 5th May 2023
Good episode? Give it some love!
Rate Episode

የ መ ን ታ ፡ እ ና ት ፡ ፖ ለ ቲ ካ

[ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ]

ለማበጠር ጀምራው ከነበር ፀጉሯ ውስጥ እጇን ወትፋ "ዋ………ይ"ብላ ጮኸች ። እሪታዋ ርዝመቱ በመሃል ቅላፄዋ እስኪለዋወጥ ነበር ። ጩኸቷን ተከትሎ ቤቱ ውስጥ ፀውታ (*ፀጥታ + ክውታ) ሰፈነ ። የድንገት ጩኸቷ ከሷ በፊት ሲርገበገቡ የነበሩ ሁለት የመንትዬ እንጥሎችን አርግቧል ።

ሣራ ያለግዜ የመጣችባት ፅጌዋ(*ፔሬዷ) ምቾት ነስታት ድምፅ የሚባል ነገር መስማት አስጠልቷታል። አንዴ አግና በለቀቀችው ጩኸቷ ያሰፈነችውን ፀውታ ቶሎ ለመጠቀም አሰበች ።

ከጆንያ ላይ ሃባ ክር መዛ ልጆቿ የተጣሉበትን ፊኛ የኮመዲኖው ጠርዝ ላይ ቋጠረችው። ድምር ለቅሷቸው ሲያስጨንቃት ወላ ፊኛውን መደንቆል ዳድቷት ነበር ።… ጧ! አርጋ አፈንድታ - ሠላሟን ያገኘች እንደው - ግን መጮህን መረጠች ።

ፊኛው ላይ እንደማይደርሱ ያወቁት አልቃሻ ልጆቿ በድንገቴ ቃጠሎ ጩኸቷ ተደናግጠው ለአፍታም ቢሆን እንደማደብ አሉ ። ለቅሷቸውን እንደፍሬን ቀጥ ማድረግ አሳፍሯቸው ነው መሰል ተንፈሳፍሰው ባላዝኖት ዋጡት ።

ረጭታውና የቤቱ ሰላም የቆየው ግን ለግማሽ ደቂቃ ነበር ። በሰማያዊው ኮመዲኖ ተደብቃባ የነበረችው እጀ'ዱሽ አሻንጉሊት (ታቲ ነው የሚሏት) ላይ አይናቸው እስክታርፍ ። አሻንጉሊቷ የተደበቀችበት ምክንያት መሳይ ጓደኛዋ (ቲታ) ጠፍታ እሷንለሁለቱም ማካፈል ከባድ ስለነበር ነው ።

ልክ ታቲን እንዳዩ የለቅሷቸው መቀጣጠያ ሌላ ጋዝ ሆነች ። ( *ሰው አይገባውም እንጂ መንታ ማሳደግ አንድአይነት ልብስ ከማልበስ የዘለለ ፖለቲካ ነው ። ዲፕሎማሲ ሳይችሉ እንዴትም የመንታ እናት አይኮንም)

* * *

ዛሬ ፥ የመንትየዎቹ ኢዛና'ና ሣይዛና አራተኛ ዓመት የልደት በዓል ነው ። አራቱ ዓመታት ምኔ እንደንፋስ እንዳለፉ ጭራሽ አታውቅም ። የእያንዳንዷ ቀን ርዝመት ግን ማለቂያ አልነበረውም ። ሌት ተኝታ ካደረችበት እንቅልፍ ባይኗ ሳይዞር ያነጋችው ይበልጣል ።

እንዲህ ያማረ ድግስ በቤቷ ስታዘጋጅ የመጀመሪያዋ ነው ። ሳምንት ሙሉ ስታስብበት ከርማ እንደሚሆን ለማድረግ አንድ ለናቷ የቀረቻትን አምሳ ብር ፈነከተች።

ቅዳሜ ደርሶ ደሞዝ እስክትወስድ መቆያ ቤስቲን እንደሌላት እያወቀች ለልደታቸው የሚሆኑ ነገሮችን ገዛዝታ እጇ ላይ የቀራት አስራ ስድስት ብር ነው ። ሆኖም ከድግሱ ኋላ ስለሚመጡ ግጥ ቀናት ማሰብ ጭራሽ አትፈልግም ።

ቲታ (አሻንጉሊቷ) የቆሰቆሰችውን ለቅሶ ገላቸውን በማጠብ ሸውዳ ከሐይቅ የታጨደ ለምለም ገሣ ትጎዘጉዝ ገባች ። መብል ከመደርደሯ ቀድማም የልብስ ሳጥኑን በመጎተት እንደጠረጴዛ የቤቱ መሃል ላይ አኖረችው ። በዘይት የተሟሸ ድስት ውስጥ የዘራችውን ፈንዲሻ በክዳኑ እንዳፈነች አፈካች ። እምትሰራበት ዳቦ ቤት ያስጋገረችውን ኲንስንስ ህብስትም አማትባ ቆራረሰች። ( * ቄስ ቢጠፋ ወንድ … ወንድ ጠፋ ተብሎ ዳቦ ሣይቆረስ አይቀር )

ይህ ሁሉ ሲሆን የተጠራ ሰው አልነበረም ። ድግሡ የቤተሰብ ነው ፤ የእማይቷና የደቋ ብቻ ። አራት አመት ዝዋይን መባጃ (*ላልቶ ሲነበብ መቆያ እንደማለት) አርጋት ስትኖር ከልጆቿ በቀር ከሰው አክርራ የገጠመችበት ግዜ አታስታውስም ። ጠፍታ እንደመምጣቷና ላገሩ አዲስ እንደመሆኗ አንገቷን አቀርቅራ ወጥታ አፏን እንደለጎመች ትመለሳለች ። ንጭንጯ - መከፋቷ -ማልቀሷ - ሚስጥሯ ፤ ሁሉም በሯን ከዘጋች በኋላ ነው ። ይሄ ፥ ጥሩ የሽቦ አጥር ሰራላት ። እንደ ስውር ክፈፍ እንግዶችን አርባ ክንድ ከሷ አራቀ ። አሁን…ያለፈ ታሪኳን የሚገምት እንጂ የሚያውቅ ባገሩ አንድ አይገኝም።

ሣራ የፅንስ አፍይ እርሾዋን ዝዋይ አልተቀበለችም ። ወደዝዋይ ከመውለዷ ስምንት ወር ቀድማ ነው የመጣችው። የመጣች ሰሞን የነበራትን ወዝ እንዲ በአራት ዓመት ረግፎ ያልቃል ብሎ የገመተ የለም ። ገላዋ - ደም ግባቷ - የፈገግታዋ ስርጉድ - ከስከሶ ፀጉሯና ድምቡሽ ቂጧ ፤ ለከተማው ገልዋዳ ሁሉ አፍ ማስከፈቻ ነበር ።

ማርገዟ እየለየ ሲመጣ - ከንፋስ እንደሻለች (*ሽል እንደያዘች) ሁሉ የአባትየውን ማንነት በሆዷ አብታ ኢዛናንና ሣይዛናን ተገላገለች። ጎረባብቶቿም በጀርባዋ ይንሾካሾኩ እንጂ ደፍረው አልጠየቋትም ። ነገሩ 'ምስኪን የማርያም አራስ' ብለው ከንፈር ከመምጠጥ ያለፈ ሙያም የላቸው ።

* * *

ለሆነ ንግስ (*ለገብርዔል መሰለኝ) ለኩሳው ግማሹ የቀለጠ ሻማን ከመስኮት ጠርዝ አውርዳ ሳጥኑ ላይ አስቀመጠች ። ይህን ያዩት ልጆቿ ለልደታችን አዲስ ሻማ ካልተገዛ የሚል ሌላ ንጭንጭ ጀመራቸው ። ንጭንጩ ወደለቅሶ ከመቀየሩ ቀድማ ወጣችና ሁለት ሻማ ገዝታ ገባች ። ስትመለስ እጇ ላይ አስራ አንድ ብር ቀራት ።

መዳህና መደገፍ ከጀመሩ ወዲህ ቀኑን ሙሉ ስትጯጯህ ነው የምትውለው ። የልጆቿ ኃይል ግን ከእርሷ በአእላፍ ይበልጣል -የመቶ ባትሪ ድንጋይ ጉልበት ነው ። ሣይዛና አልጋ ላይ ለመውጣት የተነጠፈ አልጋ ከሳበ ኢዛና በጆግ ያለ ውሃ ይደፋል ። አንደኛው የጫማ ሶል አፉ ውስጥ ሲከት አንደኛው የተጣለ ማስቲካ ፀጉሯ ላይ ይለጥፍባታል ። አንዱ ሥኳር በትኖ ከላሰ ሌላኛው ጋወኗ ላይ ኩባያ ደፍቷል ። (*እናት ስድስት እጅ ነው ያላት - ይሉት ተረት ቀልድ አይደለም)

አንዳንዴ ይደክማታል ። ድካም አይሉት ከባድ ድካም ። አለ አይደል አዙራ የለበሰችውን ቲሸርት አስተካክላ ለማድረግ ሀይል እስከማጣት ድረስ ። ይኼኔ ያለአባባይ ለሰዓት ታለቅሳለች ።በድሎት ተጨንቃ ያደገች ልጅ ሻሽ የክቷ ሆኖ ስታገኘው -በማታቀው ከተማ ያለአንድ ዘመድ ስትኖር - እናትም አባትም ስትሆን - እጣፈንታዋ ከጠርዝ ሲወጣ …እንዴት አታለቅስ ?

ይዛ የገባችውን ሻማ ለኮሰች ። የለኮሰችበትን ክብሪት ወዝውዛ አጠፋችና እንደማይክ ከአፏ በመደቀን " ክቡራትና ክቡራን የሣራ ተስፋይ ቤተሰቦች - እናታችሁ ለልደታችሁ ሲባል ከኡዝቤኩስታን ካስመጣችው ባንድ ጋር አብራ ታቀነቅናለች " አለች ።

ሣይዛና ከአፏ ተቀብሎ "ኡዝቤኩቲሲሲዛን እንደኛ መንታ አለ ? …እማዬ " ። ለመልስ ማሰቢያ ግዜ ሳይሰጣት ሌላኛውን ጥያቄ በዛው ቀጠለ ። "እኛ ግን ለምንድን'ነው መንታ የሆነው ?"

በድካም ውስጥ ሆናም ቅብጠታቸው እንጂ ጥያቄያቸው ሰልችቷት አያውቅም ። " እግዛብሄር ሁላችንንም ሲፈጥር በርሱ አምሳል ነው የሠራን - እና አንዳንዴ የሆነ ፊት ይሰራና በጣም ከወደደው… ይደግመዋል ። ከዛ … መንታ ይፈጠራል ማለት ነው ። " ወሬዋን ጨርሳም እንድትቀጥልላቸው ፊታቸውን እያብለቀለቁ ያይዋታል ። ስትወዳቸው ለጉድ ነው …አታበላልጥም ። ሳይዛና እንቅልፋም ስለሆነ ምናልባት እሱን የበለጠ ሳትወድ አትቀርም። (*ይህን ለመረዳት የመንታ እናት መሆን ያስፈልጋል)

አይን አይናቸውን እያየች "… ሃፒ በርዝ ደ…'' ከማለቷ

ከማዳበርያ በተሰራው ኮርኒስ ውስጥ የሚንሸራሸሩት አይጦች መዝሙሯን ለሁለተኛ ግዜ አቋረጧት ። እንዳልበረገገች ሁሉ ራሷን አጀግና " ለ…ሙሽሪት … ማንን ልዳርላት ? " አለቻቸው ። አውቀውባታል ፤ የሷን ያህል አይጥ የሚፈራ በቤቱ የለም ።

እንደጀርባዋ ታሪክ*(የማይነገር/የማይፃፍ) በዋነነት የምትፈራው ወንድን ልጅ ነው ። ፂም አብቃይ ሁሉ ቀንድ የቀረው አውሬዋ ነው ። የፈጣሪዋ ግፍ ይባስ ጭራሽ ሁለት ተብዓት ከማህፀኗ አሸከማት ። በሆዷ ዓመት ቀረሽ ወራት የፀነሰቻቸውን ....

---

Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

Show More
Rate

Join Podchaser to...

  • Rate podcasts and episodes
  • Follow podcasts and creators
  • Create podcast and episode lists
  • & much more

Episode Tags

Do you host or manage this podcast?
Claim and edit this page to your liking.
,

Unlock more with Podchaser Pro

  • Audience Insights
  • Contact Information
  • Demographics
  • Charts
  • Sponsor History
  • and More!
Pro Features