Ethiopian History and Political Economy Podcasts Host
የኢትዮጵያ ታሪክ ሐሪ አትክንስ እንደፃፈውስለ መፅሐፉበ62 ገፆች ውስጥ ከቅድመ ክርስቶስ 1500 ዓመት እስከ 1962 ዓ/ም (እ/ኤ/አ) ያለውን  የኢትዮጵያን ታሪክ ይተርካል። የታተመበት ቋንቋ እንግሊዘኛ ሲሆን በ1969 ሴንትራል ማተሚያ ቤት ታትሟል። አኔ የምቃኘው የአማርኛ ትርጉሙን ሲሆን ተርጓሚ ማን እንደሆነ አይገልፅም። History of Ethiopia from 1500 BC to about 1962. 62 pages. Paperback: 62 pages ፥ Publisher: Central Press (1969) ፥ Language: Englishስለ ፀሐፊው :- ሐሪ አትኪንስ (Harry Atkins)ፀሐፊው ስለሱ የተፃፉ ብዙ ፅሁፎችን አላገኘሁም። ሆኖም ከአንድ የኮሌጅ ድህረ-ገፅ ላይ እንደተረዳሁት ሰውየው በኢትዮጵያ ፍቅር የጦዘ ከመሆኑም በላይ ለኢትዮጵያ ብዙ ውለታን ውሏል። በተጭማሪም አራት ኢትዮጵያውያን ልጆች አሉት። ቀጥሎ ባለው ሊንክ በመግባት በጥልቀት ስለሱ ማንበብ ይችላሉ። (https://www.westmont.edu/enchanted-ethiopia )ከዚህ መፅሐፍ ባሻገር ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዙ ሌሎች መፅሐፍቶችን ፅፏል። እነዚህ የሚከተሉት ናቸው።A Geography of Ethiopia January 1, 1970History of Africa (from Ethiopian perspective) January 1, 1974Ethiopia: Land of enchantment January 1, 1975ሁሉም መፅሐፎች አማዞን ላይ ይገኛሉ። እኔ "Ethiopia: Land of enchantment January 1, 1975” አዝዣለሁ። በነገራችን ላይ ይህኛው ስመ ጥር የሆነ መፅሐፋቸው ነው።ስለ መፅሐፉየኢትዮጵያን ታሪክ በሰባት ምዕራፎች ከፋፍሎ ይመለከታል። የኢትዮጵያ ታሪክ ፡ የቀድሞ ዘመናትየኢትዮጵያ ታሪክ ፡ መካከለኛ ዘመንየኢትዮጵያ ታሪክ ፡ 16 እና 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመንየኢትዮጵያ ታሪክ ፡ ኢትዮጵያ እና አውሮፓየኢትዮጵያ ታሪክ ፡ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክየኢትዮጵያ ታሪክ ፡ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያየኢትዮጵያ ታሪክ ፡ የዛሬይቱ ኢትዮጵያየአማርኛ ትርጉሙ የግዕዝ ቁጥሮችን ተጥቅሟል። አነዚህን ቁጥሮች ወደ አረብ ቁጥሮች ለመቀየር “Geez Numbers” የተባለ የሞባይል አፕሊኬሽን ተጠቅሜለሁ። 26 የሚጠጉ ስዕሎች በመፅሐፉ ውስጥ ይገኛሉ። ስለዚህ እያንዳናዱን ክፍል በተለያየ “ኢፕሶድ” እቃኘዋለሁ። ኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያዊ፥ ኢትዮጵያውያን ለሚሉት ርዕሶች ጥሩ መንደርደሪ ሊሆን ይችላል የሚል እምነት አለኝ። 
S00 :- ኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያዊ፥ ኢትዮጵያውያን መንደርደሪያE03 :- የዛሬዋ ኢትዮጵያ የጥንቷም ኢትዮጵያ ናትክፍል ሶስት : እኔ ምን ተማርኩበት?-      ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ታሪክ የጥንት ጥቁር ህዝብ ታሪክ የመጨረሻው ቅሪት ነው ፡፡ (Ethiopia and the History of Ethiopia is the last remnant of the history of the ancient black’s people. )-      ኢትዮጵያ እና ሱዳን አንድ ሀገር ነበሩ ፡፡ (Ethiopia and Sudan were one country.)-      ሀገር ማለት መሬቱ ሳይሆን ህዝብ ነው ፡፡ ተብለን ልጅ እያለን የተማርነው ትምህርት አሁን ለምን እንደሆን ገብቶኛል። (A country is not the land but the people. I understand why we learned what we learned as children.)-      ቀለማችን የመነጨው ከኖርበት አካባቢ ነው ፡፡ ሰለዚህ ሰው መሆናችን ከቀለም ወይም ከዘር የበለጠ አስፈላጊ ነው ፡፡ ምክንያቱም አንድ ዘር አለ ፣ የሰው። የቀረው ሁሉ ውሸት ነው። (Our color comes from where we live. So being human is more important than color or race. Because there is one race, man. Everything else is a lie.)
S00 :- ኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያዊ፥ ኢትዮጵያውያን መንደርደሪያE02 :- የዛሬዋ ኢትዮጵያ የጥንቷም ኢትዮጵያ ናትክፍል ሁለት:- "ጉድ ኒውስ ባይብል" (GNB - Good News Bible) ለምን ኢትዮጵያን በሱዳን መተካት ፈለገ? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ የሰጠችው ምላሽ እና ያደረገችው ትግል? ጉዳዩ በምን ተቋጨ? የሚሉት ጥያቄዎች በዚህ ክፍል ምላሽ አግኝተዋል።Why did the Good News Bible (GNB - Good News Bible) want to replace Ethiopia with Sudan? The Ethiopian Orthodox Church's Response and Struggle? How Did It End? all this question got answered.
ይህንን ድምፅ ከሰሙ በተለያየ መንገድ ወይም አጋጣሚ እዚህ ጣቢያ ደርሰዋል ማለት ነው። እንኳን ደህና መጡ። በዚህ የራዲዮ ጣቢያ ወይም ፖድካስት የሚተላለፉ መልዕክቶች ለሰሚው ማትረፊያ እንደሚሆኑ እምነታችን ነው።የዚህ ፖድካስት አዘጋጅ እና አቅራቢ ኤፍሬም አይፎክሩ ሰለሞን እባላለሁ። የሪቪል መፅሔት ዋና አዘጋጅ ነበርኩ፤ እንዲሁም በተለያዩ የህትመት ሚዲያዎች ላይ በተለያየ የስራ ዘርፍ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ተሳትፋለሁ። የመጀመሪያ ዲግሪዬን በኢኮኖሚክስ ሰርቻለሁ፤ በተጭማሪም በዚህ ወቅት ማስተርስ ዲግሪዬን እየተከታተልኩ እገኛለሁ። ሚስት አግብቻለሁ።ይህንን ስርጭት ለመጀመር ያነሳሳኝ ዋነኛ ምክንያት ለራሴ እንደዚህ አይነት ዝግጅት ፈልጌ ማግኘት ስላልቻልኩ ሲሆን ሁሌም የመጀመሪያው አድማጭ እኔው እራሴው ነኝ ማለት ነው። ዝግጅቶቹ ለሁሉም ሰው ላይጠቅሙ ይችላሉ። ሊጠቅመው ለሚችል ሰው ግን እጅግ በጣም እንደሚጠቅመው አልጠራጠርም።ዓለማችን በታሪኳ የቴክኖሎጂ ማማ ላይ የደረሰችበት እንደዚህ ያለ ዘመን ኖሮ አያውቅም። በተለይ የመረጃ ፍሰት መጠን አድጓል። መረጃን የሚሰበስቡ እና ማሰራጨት የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች በእያንዳንዱ ግለሰብ እጅ እየገባ ይገኛል። ሆኖም በዚህ ወቅት እየተፈጠሩ ባሉ ክስተቶች ላይ ግን መግባባት አልቻልንም። ብዙ መረጃ እና ማስረጃ ብዙ መግባባትና አንድነት ላይ አላደረሰንም።ስለዚህ ያልመረጥነውን ብንሰማም የመረጥነውን ግን መቀበል እንችላለን። የመረጥነውን ማመን እንችላለን። ያመነው ታሪካችን ይሆናል። ምክንያቱም ታሪካችን የተቀበልነው ነው፤ ታሪካችን የምንገነባው ነው፤ ታሪካችን የምንተርከው ነው።የኢትዮጵያን ታሪክ ኢትዮጵያውያን ይቀበሉት፤ ኢትዮጵያውያን ይምረጡት፤ ኢትዮጵያውያን ይገንቡት፤ ኢትዮጵያውያን ይተርኩት። ሰው ምንም እንኳ እውነት ብትነግረው የሚያምነው የፈለገውን ነው። ስለዚህ ሌላው ስለኛ ስለሚያምነው ሳይሆን እኛ ስለራሳችን የተቀበልነው ታሪክ ዋጋ አለው።ስለዚህ በዚህ “ፖድካስት” እና ተያያዥ ስራዎቻችን የምናደርገው ይህንን ነው።የዝግጅቱ አቀራረብ በ “ ሲዝን (S)" - ዋናው መነሻ ርዕስ ወይም ሃሳብ፥ “ ኤፕሶድ(E)" በዋናው ርዕስ ስር ያሉ ንዑስ ርዕሶች እና ሀሳቦች ሲሆኑ እና በዚያ “ ኤፕሶድ" ስር ያሉ ዝግጅቶች ደግሞ በ”ፓርት(P)” የተደራጁ ናችው።ለምሳሌ የመጀመሪያው-      “ሲዝን (S01)” “ኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያዊ፥ ኢትዮጵያውያን መንደርደሪያ” የሚል ርዕስ ሲኖረው-      የመጀመሪያው “ኤፕሶድ(E01)” - "የዛሬዋ ኢትዮጵያ የጥንቷም ኢትዮጵያ ናት” የሚል ይሆናል።-       በዚህ ስር ያለው የመጀመሪያው ክፍል ወይም “ፓርት(P01)” ደግሞ - ኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያዊ፥ ኢትዮጵያውያን መንደርደሪያ የሚል ነው።ማስታወሻ፦ በዚህ ቻናል ላይ የሚተላለፉ ዝግጅቶች በሌላኛው (IPedX Ethiopia) ቻናል ላይ በድጋሚ ተጭነው ሊገኙ ይችላሉ። ዝግጅቶቻችን በየትኛው የፖድካስት እና ሙዚቃ መስሚያ “አፕልኬሽን” ላይ ይገኛል።
View 6 more appearances
Share Profile
Are you Ephrem? Verify and edit this page to your liking.

Share This Creator

Recommendation sent

Join Podchaser to...

  • Rate podcasts and episodes
  • Follow podcasts and creators
  • Create podcast and episode lists
  • & much more

Creator Details

Birthdate
May 6th, 1993
Location
Melbourne, Victoria, Australia
Episode Count
5
Podcast Count
1
Total Airtime
1 hour, 23 minutes
PCID
Podchaser Creator ID logo 840515